Skip to main content

ኢትዮጵያ!ታላቅ ሕዝብ እና ታላቅ ሐገር!

ኢትዮጵያ!ታላቅ ሕዝብ እና ታላቅ ሐገር!

1 ከ እስራኤላውያን ውጪ ያለ ታላቅ ህዝብ ፡-ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዊው ዝሪ አንድ ሚልዮን ሰራዊትና ሶስት መቶ ሰረገሎችን ይዞ ወደ እስራኤል ዘመተ በዚህም የተደናገጠው የእስራኤል ንጉስ ወደ ፈጣሪው ጽሎት አደረሰ ጸሎትም ሲያደርስ ኢትዮጵያውያኑን " ታላቅ ሕዝብ " በማለት ጠራቸው እንግሊዘኛው መጽሀፍ ቅዱስ ይሄንን ሲተርጉመው " The Great Ethiopians " The Great Nation " በማለት ነው፡፡

“ኢትዮጵያዊውም ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰዎችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ይዞ ወጣባቸው ወደ መሪሳም መጣ። አሳም ሊጋጠመው ወጣ፥ በመሪሳም አጠገብ ባለው በጽፋታ ሸለቆ ውስጥ ተሰለፉ። አሳም። አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ሕዝብ ላይ መጥተናልና እርዳን አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ ሰውም አያሸንፍህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።" (2መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 14:9 -11)

ታላቅ ሕዝብ የሚለውን ያዙልኝ

2.የሙሴ በኢትዮጵያ ላይ መሾም 

የአይሁድ ፣ የክርስትናና የታሪክ ሊቃውንት ደግሞ በሙሴና በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚደንቅ ታሪክ አላቸው:: አይሁዶች "ሙሴ ኢትዮጵያ ሄዶ ኢትዮጵያን አርባ አመት ገዝቷል" ብለው ሲከራክሩ የክርስትናና የታሪክ ሰዎች ደግሞ " ኢትዮጵያ ላይ እግዚአብሔር ሊሾመው ነበር እንጂ የኢትዮጵያ ንጉስ አልነበረም " ይላሉ።
የክርስትና ሊቃውንት የሚጠቅሱት አንዱ መከራክርያ ይሄ ነው። ሙሴ ሲና ተራራ ላይ በቆየ ወቅት እስራኤል የጥጃ ጣኦት አቁመው ለጥጃው መስገድ ጀመሩ:: እግዚአብሔርም በዚህ በጣም ተቆጣ:: ሕዝቡንም ሊያጠፋው እንደወደደና ሙሴንም ለሌላ ታላቅ ሕዝብ መሪ እንደሚያደርገው ገለጸለት ። ይሔ ከእስራኤል ውጭ ያለ ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን ነበር?

“እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ከግብፅ ምድር ያወጣኸው ሕዝብህ ኃጢአት ሠርተዋልና ሂድ፥ ውረድ። ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ለራሳቸው አደረጉ፥ ሰገዱለትም፥ ሠዉለትም። እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አሉ ፤ሲል ተናገረው እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እኔ ይህን ሕዝብ አየሁት፥ እነሆም አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነው።አሁንም ቍጣዬ እንዲቃጠልባቸው እንዳጠፋቸውም ተወኝ አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው።” (ዘጸአት 32 ፡7-10)

ይሔ ከእስራኤል ጋር የሚወዳደር ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን እደሆነ ጻድቅ የነበረው የእስራኤል ንጉስ ቀድሞ ተናግሮታል(2መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 14:9):: በዘመነ ብሉይ የነበረው ነብዩ አሞጽም የተናገረው ይጠቀሳል ። "የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን ልጆቼ አይደላችሁምን?”(ትንቢተ አሞጽ 9፣7 )
ስለዚህ ሙሴ ሊሾምበት የነበረው ታላቅ ሕዝብ ኢትዮጵያ እንደነበረች ጥርጥር የለውም::

የሚደንቀው ግን የእስራኤላውያኑ እይታ ነው። የእስራኤላውያን የቀደሙ የታሪክ ሊቆቻቸውን ዜና መዋእል በመጥቀስ " ሙሴ ኢትዮጵያን አርባ አመት ገዝቷታል" ይሉናል። ይህንንም የጂውሽ ኢንሳይክሎፒዲያ (The Jewish Encyclopedia: A Descriptive Record of the History ..., Volume 9, page 48 edited by Isidore Singer, Cyrus Adle)ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡

3. የመጀመርያዋ የእስራኤል ቀዳማዊ እመቤት የሙሴ ሚስት ኢትዮጵይዊቷ ሲፓራ ነበረች።

ኢትዮጵያን አትንኩ !!!

ከመጽሀፍ ቅዱስ እንደምንረዳው ሙሴ በምድር ሁሉ ካሉት ሰዎች " እጅግ ትሁት " እንደነበረና ( ዘኁ 12:3) በምድር ካሉ ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር አፍ ለአፍ እንደሚናገረውና የእግዚአብሔርንም መልክ ያየ ብቸኛው ጻድቅ እንደነበረ በሚገባ ተገልጿል።( ዘኁ 12:8) ታድያ ይህ ቀረህ የማይባለው ጻድቅና የሕግ መምህር ሙሴ መርጦ ያገባት ኢትዮጵያዊቱ ሲፓራን ነው። 
በዚህም እስራኤላዊያኑ በማያገባቸው ነገር ገብተው ተናደዱ።ሊቀ ካህናቱ አሮንና ማርያም በይፋ ቁጣቸውን ገለጹ። ግን ምን ያደርጋል:: ሙሴ እንዴት ኢትዮጵያዊቷን ያገባል ብላ ያንጎራጎረችው ማርያም ስለዚህ ድፍረቷ በለምጽ ተቀጣች። ኢትዮጵያን አትንኩ !!!

"ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ። እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ።ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፥ እንደ አመዳይም ነጭ ሆነች አሮንም ማርያምን ተመለከተ፥ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር። አሮንም ሙሴን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ስንፍና አድርገናልና፥ በድለንማልና እባክህ፥ ኃጢአት አታድርግብን።" (ኦሪት ዘኍልቍ 12: 1-12)

4. የኢትዮጵያዊቷ ሲፓራ ልጆች 

ሙሴ ከኢትዮጵያዊት ሚስቱ ሁለት ልጆችን ወለደ:: እነዚህም ልጆች ስማቸው ጌርሳምና አልዓዛር ነበሩ::
“በዚያን ጊዜ የሙሴ አማት ዮቶር መልሶአት የነበረውን የሙሴን ሚስት ሲፓራን ሁለቱንም ልጆቿን ወሰደ።”(ዘጸ 18:2 )

እነዚህ ልጆች ሲያድጉ ባለስልጣን ሆነው ተሾሙ:: ቁጥራቸውም ታቦተ ጽዮንን ከሚያገለግሉት ከነገደ ሌዊ ሆነ::

"የእግዚአብሔርም ሰው የሙሴ ልጆች በሌዊ ነገድ ተቈጠሩ።የሙሴ ልጆች ጌርሳምና አልዓዛር ነበሩ።የሙሴ ልጅ የጌርሳም ልጅ ሱባኤል በቤተ መዛግብት ላይ ተሾሞ ነበር።"

ከነገደ ሴምና ከኢትዮጵያውያን ተወልደው በ እስራኤል ላይ ባለስልጣን የሆኑ የመጀመርያ ነጭና ጥቁሮች ( መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 23:14-16)

5. እስራኤልን ከግብጽ ወደ ኢየሩሳሌም እየመራ የወሰዳቸው ኢትዮጵያዊው ኦባብ

ሙሴ እስራኤልን ባሕር ከፍሎ ያሻገረ ታላቅ ነብይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ግን ሌላ የሚገርም ታሪክ ተጽፏል። ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ያሻገረው ታላቁ ነብይ ወደ ኢየሩሳሌም ሕዝቡን ይዞ የሚሄድበት መንገድ ጠፋው። ምንም እንኳን ቀን በአምደ ደመና ሌት ደግሞ በአምደ ብርሃን እየተመራ ሕዝቡን ይዞ ቢጓዝም ለሙሴ ሌላ ሰው መንገዱን ያሳያው ዘንድ ግድ ነበር። ይሄውም ሰው ኢትዮጵያዊው ኦባብ ራጉኤል ይባላል:: ሙሴ በራሱ አንደበት እንተ ለኛ ለእስራኤላውያን " አይኖቻችን ነህ " ብሎ የመሰከረለትና ሕዝበ እስራኤልን ይዞ ኢየሩሳሌም ያገባቸው ፣ ታቦተ ጽዮንንም ማደርያዋን ያዘጋጅ የነበረ ሃያል ኢትዮጵያዊ :: የኢትዮጵያዊቷ የሙሴ ሚስት ወንድም ኦባብ ወልደ ራጉኤል

"ሙሴም የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፦ እግዚአብሔር፦ ለእናንተ እሰጠዋለሁ ወዳለው ስፍራ እንሄዳለን እግዚአብሔር ስለ እስራኤል መልካምን ነገር ተናግሮአልና አንተ ከእኛ ጋር ና፥ መልካምን እናደርግልሃለን አለው። እርሱም፦ አልሄድም፥ ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ አለው። እርሱም፦ እባክህ፥ በምድረ በዳ የምንሰፍርበትን አንተ ታውቃለህና፥ እንደ ዓይኖቻችንም ትሆንልናለህና አትተወንከእኛም ጋር ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛ ለአንተ እናደርጋለን አለ።ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድርበትን ስፍራ ይፈልግላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ቀደማቸው።"(ዘኁ 10:29-33)

ታላቂቷ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

ምንጭ፡-http://zeaddisu.blogspot.com/2013/01/blog-post.html

Comments

Popular posts from this blog

Ghosting

Ghosting is to cease communications without notification. The use of the word "ghost" as a verb originated in social media in reference to dating, but the term is now used by employers to describe employees and potential employees who suddenly disappear. Typically, ghosting is used to describe: Job candidates who suddenly stop responding to messages. New hires who fail to show up for their first day of work. Employees who do not show up for a shift. Employees who leave work in the middle of the day and never come back. Some analysts blame ghosting on millennial entitlement. The reasoning is that members of the millennial generation have been brought up to feel they are special -- so special, in fact, that they do not need to follow conventional rules of behavior. Other analysts, however, maintain that ghosting behavior stems from changes in the job market and the phenomenon is simply a reflection of the laws of supply and demand in a healthy jo...

Data deduplication

Data deduplication -- often called intelligent compression or single-instance storage -- is a process that eliminates redundant copies of data and reduces storage overhead. Data deduplication techniques ensure that only one unique instance of data is retained on storage media, such as disk, flash or tape. Redundant data blocks are replaced with a pointer to the unique data copy. In that way, data deduplication closely aligns with incremental backup, which copies only the data that has changed since the previous backup. For example, a typical email system might contain 100 instances of the same 1 megabyte (MB) file attachment. If the email platform is backed up or archived, all 100 instances are saved, requiring 100 MB of storage space. With data deduplication, only one instance of the attachment is stored; each subsequent instance is referenced back to the one saved copy. In this example, a 100 MB storage demand drops to 1 MB. Target vs. source deduplication Data deduplica...

A Graphics Processing Unit (GPU)

A graphics processing unit (GPU) is a computer chip that performs rapid mathematical calculations, primarily for the purpose of rendering images. A GPU may be found integrated with a central processing unit (CPU) on the same circuit, on a graphics card or in the motherboard of a personal computer or server. In the early days of computing, the CPU performed these calculations. As more graphics-intensive applications such as AutoCAD were developed; however, their demands put strain on the CPU and degraded performance. GPUs came about as a way to offload those tasks from CPUs, freeing up their processing power. NVIDIA, AMD, Intel and ARM are some of the major players in the GPU market. GPU vs. CPU A graphics processing unit is able to render images more quickly than a central processing unit because of its parallel processing architecture, which allows it to perform multiple calculations at the same time. A single CPU does not have this capability, although multi...